ኮምፒውተር ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የሚያጋጥም ህመም…

ኮምፒውተር እንዴት እንጠቀም

አብዛኛውን ጊዜያችንን ኮምፒውተር ላይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ የምናሳልፍ ከሆነ ለተለያዩ ችግሮች ልንጋለጥ እንደምንችል በተለያየ ጊዜያት ተነግሯል።
በስራ ገበታችን ላይ ስንሆን አብዛኛውን ጊዜያችንን በኮምፒውተር ላይ የምናሳልፍ ከሆነና እንደ የራስ ምታት፣ የአይን መድረቅ፣ የማቃጠል እና ብዥታ ከተፈጠረ እንዲሁም የአንገት ህመም ከተሰማን “የኮምፒውተር እይታ ህመም ነው” ይሉናል ተመራማሪዎች።

የኮምፒውተር እይታ ህመምን ለማከም1. ከኮምፒውተር እይታ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የህመም ስሜትን ለማከም በየ 20 ደቂቃ ልዩነት ለ20 ሰከንድ አይናችንን ከኮምፒውተራችን ላይ በማንሳት እረፍት ማድረግ ይኖርብናል። በዚህ ጊዜም በአካባቢያችን እስከ 6 ሜትር ርቀት
ውስጥ የሚገኙ ነገሮች ላይ ማተኮር መልካም ነው ።
2. አይናችንን ማርገብገብ
አብዛኛውን ጊዜ ከኮምፒውተር ስክሪን ጋር በምናሳልፍበት ጊዜ አይናችንን በመደበኛ ሰዓት ከምናርገበግብበት በታች ነው የምናርገበግበው።
ይህ ደግሞ አይናችን ተገቢውን እንቅስቃሴ ባለማድረጉ ለአይን ድርቀት እና ማቃጠል ለመሳሰሉት ችግሮች ሊዳርገን ይችላል።
ስለዚህ በኮምፒውተር ላይ አትኩረን ስራችንን በምንሰራበት ጊዜ በተቻለን መጠን አይናችንን ቶሎ ቶሎ ማርገብገብ ይኖርብናል።


3. መነፅር መጠቀም
በአሁኑ ጊዜ በብዛት ገበያውን የተቆጣጠሩት ፍላት የኮምፒውተር ስክሪኖች ብርሃን መቀነሻ ተጨማሪ መስታወት ያልተሰራላቸው በመሆኑ ከኮምፒውተሩ ላይ የሚመጣው ጨረር ቀጥታ ከአይናችን ጋር በመገናኘት አይናችን ላይ ጉዳት ሊያስከትልብን ይችላል።
ስለዚህም ባለሙያ በማማከር ጨረር ሊከላከሉልን የሚችሉ መነፅሮችን መጠቀም ይመከራል።
4. በኛ እና በኮምፒውተራችን መካከል ርቀት እንዲኖር ማድረግ
ስራችንን በምንሰራበት ጊዜ በእኛ እና በኮምፒውተራችን መካከል ያለው ርቀት ለጤናችን ወሳኝነት አለው። በተለይም ኮምፒውተሩን ከአይናችን ትይዩ ዝቅ አድርገን መስራት ምቾት እንዳለው ነው የሚነገረው።
ስለዚህም ኮምፒውተራችን ከአይናችን ትይዩ ከ10 እስከ 15 ሴንቲ ሜትር ዝቅ ብሎ እንዲቀመጥ ማድረግ መልካም ነው።
እንዲሁም በኮምፒውተራችን እና በፊታችን መካከል ያለው ርቀት ደግሞ ከ46 እስከ 66 ሴንቲ ሜትር ርቀት እንዲኖር ይመከራል።

Discover more from Mahidere Tsibeb

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading

Design a site like this with WordPress.com
Get started