
ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በፓትርያርኩ ላይ ክፉ የሚናገር እየተዳፈረ ያለው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ነው ሲሉ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገለፁ።
ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰሞኑን ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጉዞ ጋር እየተነሱ ያሉ ጉዳዮች ላይ ለሚዲያዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ ባልተጨበጠ ነገር ክፉ ቃል ሊነገር አይገባም ሲሉ ተናግረዋል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሕክምና ወደ አሜሪካ በሚሔዱበት ጊዜ ይዘውት የሚሔዷቸውን ሁለት ጽላቶች እንዲዘጋጁ በልዩ ጽሕፈት ቤታቸው በኩል መታዘዙን ያስታወሱት ብፁዕ አቡነ አብርሃም እርሳቸውም በቅርጻ ቅርጽ ማዘጋጃ ክፍል እንዲዘጋጅ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ነገር ግን በማኅበራዊ ሚዲያ “ቅርጻ ቅርጽ” የሚለውን “ቅርሳ ቅርስ” ብለው በመውሰድና ያልተገባ ትርጉም በመስጠት ቅዱስ ፓትርያርኩ ቅርስ ሊያሸሹ ሲሉ እንደተያዙ በማስመሰል ስማቸውን ለማጠልሸት የሔዱበትን ርቀት እርሳቸውን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ክብር የሚነካ ነው ብለው ገልጸውታል።
አክለውም ቅርስ መጠበቅን ለቤተ ክርስቲያን ማስተማር አይቻልም ያሉ ሲሆን አባቶቻችን በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ነው ቅርሶችን ከትውልድ ወደ ትውልድ ያስተላለፉት ብለዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ መንግስት ቅርሶች ከሃገር እንዳይወጡ መቆጣጠር አለበት ያሉ ሲሆን ለወደፊት እንዲህ ዓይነት ችግር እንዳይፈጠር እንሠራለን ብለዋል። ቤተ ክርስቲያን ላይ ያልተገባ ነገር ሲናገሩ የነበሩ ሰዎችም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ምንጭ:- ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ
የተዋህዶ ሚዲያ አማራጮች
የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCKqL7UekDOyp6q4j7ObVf9Q
የቴሌ ግራም ቻናል ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ https://t.me/tewahedomediacenter
አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/
የኢንስታግራም ገጽ ይከታተሉ
http://www.Instagram.com/tewahedo_media
Leave a comment