ገላውዲዎስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ እናስተዋውቃችሁ፡-



የገላውዲዎስ ቤተ-ክርስቲያን በገላውዲዎስ ቀበሌ አስተዳደር ስር
የሚገኝ ሲሆን ቀበሌው ስሙን ያገኘው በዚሁ ቤተክርስቲያን ስም
እንደሆነ ይነገራል ፡፡
የሰማእቱ ቅዱስ ገላውዲወስ ቤተ-ክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ዞን
በደራ ወረዳ አፈር ውኃ እናት በገላውዴዎስ ቀበሌ ይገኛል፡፡ ይህ ቤተክርስቲያንከአርብ ገበያ ከተማ ወደ እስቴ
ሲጓዙ ከ10 ኪሎ ሜትር ጉዞ በኃላ ይገኛል ፡፡ 4 ማዕዘን ቅርፅ
ያለውና 3 ጉልላት ያሉት የገላውዴዎስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተው ከ1540-1559 እ.ኤ.አ በኢትዮጵያ በነገሱት በአፄ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግስት ነው ፡፡

የገላውዲዮስ ቤተ ክርስቲያን በ Google mape


የስሙ አወጣጥ ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ድርሳናትም ይናገራሉ ፡፡
የአፄ ልብነድንግል ልጅ የሆኑት ንጉስ ገላውዴዎስ የግራኝ መሐመድ ግፍ ባንገፈገፋቸው ጊዜ ብዙ ሰራዊት ብዙ ግመሎችና የሰማዕቱ ገላውዴዎስን ታቦት ይዘው ዘመቱ፡፡ ወደ አሁኑ የገላውዴዎስ ቀበሌ ከአሁኑ የገላውዴዎስቤተክርስቲያን ከተመሰረተበት እረጅም ተራራ ላይ በደረሱ ጊዜ ግመሎቻቸው ደከሙባቸው የያዙትን ጦር ይዞ መቀጠል ተስኗቸው ለያዙት ታቦተ ብፅአት ገቡ (ስለት ተሳሉ) “ግራኝን ድል ለማድረግ ብታበቃኝ ቤተክርስቲያንክን ከዚህ ቦታ ሰርቸ አስቀምጣለሁ” የሚል ፡፡ የደከሙ ግመሎቻቸውንና ሰራዊታቸውን ይዘው ወደ ሰሜን ጎንደር አቀኑ ፡፡ በለስም ቀናቸውና በአሁኑ ሰዓት “ግራኝ በር” በተባለው ቦታ
ላይ ሲደርሱ ግራኝ መሐመድን ድል አደረጉ፡፡ ቃላችውንም ሳያፈርሱ በቦታው የታቦተ ገላውዴዎስ ቤተክርስቲያን ተከሉት ፡፡ ብዙ ግመሎችና አገልጋዮችን የስጦታ እቃዎችንም በዚያው አስቀምጠዋል ፡፡ በቦታው ረጅም ዘመን ያላቸው ታሪካዊ
ቅርሶች፣ንዋየ ቅዱሳትና በተለያዩ ነገስታት የተበረከቱ ስጦታዎች ይገኛል ፡፡ ከነዚህም መካከል የአፄ ቴዎድሮስ ምንጣፍና መከዳ (ትራስ)የአጼ ገላውዴዎስ ቀንደ መለከትና ሰናፊ (ፈረስ ላይ
ሲቀመጡ የሚለብሱት) የግራኝ መሐመድ ካባ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ፡፡
ቤተክርስቲያኑን ልዩ የሚያደርጉት ሁኔታዎች፡-
ሴቶች በቤተክርስቲያን ስርዓት በስተደቡብ ወንዶች ደግሞ
በስተሰሜን የቀብር ስርአት ይፈፅማል ፡፡

በሳጥን ወይም በግንብ (በኃውልት) መቅበር ግን
አይፈቀድም ፡፡ ነገር ግን የቀብር ጥበት ብሎ ችግር በቤተክርስቲያኑ አይታሰብም ።ለምን ቢሉ የአንድ ሰው እሬሳ ከተቀበረ ከወር በኃላ የት እንደሄደ አይታወቅም ፡፡
ሁለተኛው አስገራሚ ጉዳይ ደግሞ ቤተክርስቲያኑ ሲመሰረት አብራ የገባችና አሁን ድረስ በግቢው በር በቀኝ በኩል የምትገኝ ንብ ናት ፡፡ የሚያስገርመው እንደ ሐይማኖት አባቶች አባባል ይህን ያህል እድሜ ስትቆይ የማትራባ መሆኗ ነው ፡፡
የምትሰጠውን ማር ለህሙማን ፈውስ ተብሎ ብዙዎቹ
እንደሚጠቀሙበት ብዙ ነዋሪዎች ይናገራሉ ፡፡

ሊቀጳጳስ ብጹዕአቡነ ኤልሳዕ

የቅዱስ ገላውዲዎስ ክብረ-በአል ታህሳስ 11 በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ፡፡ አንጋፉው የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የነበሩት ብጹዕአቡነ ኤልሳዕ ስርዓተ ቀብራቸው በኑዛዜ ቃላቸው በተናገሩት መሠረት፣ በተወለዱበት ደራ ወረዳ አፈር ውኃ እናት ( ገላውዲዮስ ቀበሌ ) በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ_ቤተ ክርስቲያን በ 20-09-2011 ዓ/ም በክብር አርፏል ፡:

Discover more from Mahidere Tsibeb

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading

Design a site like this with WordPress.com
Get started