አርሰናል አሌክሳንደር ዚንቼንኮን ማስፈረማቸውን ይፋ አደረጉ !

አሌክሳንደር ዚንቼንኮን

አርሰናል የ 25 ዓመቱን የኋላ መስመር ተጫዋች አሌክሳንደር ዚንቼንኮን ከማንችስተር ሲቲ ማስፈረማቸው ይፋ ሆኗል ።

ለዝውውሩ ወደ ሰላሳ ሁለት ሚልዮን ዩሮ ወጪ እንደሆነ ሲገለፅ ቀድሞ በሲቲ ቤት ከሚያውቀው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ጋር ዳግመኛ አብሮ የመስራት ዕድልንም አግኝቷል ።

የሀያ አምስት አመቱ ዚንቼንኮ በዚህ ሳምንት ሁለት የጤና ምርመራዎችን አድርጎ በተሳካ ሁኔታ ሲያልፍ የሚቀጥሉትን አራት አመታት በአርሰናል የሚያቆየውን ውል እንደተፈራረመ ተገልጿል ።

ዚንቼንኮ በተከላካይ መስመር እንዲሁም በመሀል ሜዳ ስፍራ ላይ መጫወት የሚያስችል ብቃት ያለው ተጫዋች መሆኑ ይታወቃል ።

ዚንቼንኮ በማንቸስተር ሲቲ ፕሪሚየር ሊጉን እና ካራባኦ ዋንጫን አራት አራት ጊዜ ሲያነሳ አንድ ጊዜ ደሞ የኤፌ ኤ ካፕ ዋንጫን አሳክቷል ።

መድፈኞቹ ከዚህ ቀደም ከማንችስተር ሲቲ አጥቂውን ጋብርኤል ጄሱስን ማስፈረማቸው ይታወሳል ።

መድፈኞቹ በዝውውር መስኮቱ አስቀድሞ ጋብሬል ጄሱስ ፣ ማርኪኖህስ ማት ተርነር እና ፋቢዮ ቬራ ማስፈረማቸው የሚታወስ ነው ።

አርቴታ እና አሌክሳንደር ዚንቼንኮ

የልጅነት ህልሜ እውን ሆኗል “

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሌክሳንደር ዚንቼንኮ መድፈኞቹን መቀላቀሉ ደስተኛ እንዳደረገው በሰጠው አስተያየት ተደምጧል ።

” የቡድን ስብስቡን ስለተቀላቀለ ደስ ብሎኛል አሌክስን ከዚህም በፊት በደንብ አውቀዋለሁ ፣ ከሲቲ ከተለያየሁ በኋላም ስፈልገው ነበር ጥሩ ብቃት ያለው ተጫዋች ሲሆን ለቡድናችን ጥራትን ይጨምራል ።

በተለያዩ ስፍራዎች መጫወት መቻሉ ለቡድኑ የማጥቃትም ሆነ የመከላከል ስራ እንደሚያግዘን አምናለሁ ፣ እንደ ግለሰብም አሌክስ ጥሩ ስብዕና ያለው ተጫዋች ነው ” ሲል አርቴታ ሀሳቡን አካፍሏል ።

ዚንቼንኮ በበኩሉ ” በመጀመርያ የልጅነት ህልሜ እውን ሆኗል ፣ ልጅ እያለሁ የአርሰናል ደጋፊ ነበርኩ በተለይ ቴሪ ሄንሪ እና ወጣቱ ሴስክ ፋብሪጋስ ሲጫወቱ ማየት ያስደስተኝ ነበር ” ሲል ተደምጧል ።

Discover more from Mahidere Tsibeb

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading

Create your own website, free on WordPress.com.Create your own website.
Start free