አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ (proposal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች


❖አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ (proposal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
A) ማውጫ (Table of contents)
B) አጭር መግለጫ (Executive Summary)
C) መግቢያ (Back Ground)
D) ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች (Rationale)
E) የፕሮጀክቱ ዓላማ (project objective)
F) የፕሮጀክቱመግለጫ (project Description)
G) የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት (project management and organization)
H) የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮችና ተጠቃሚዎች (stakeholders and Beneficiaries)
I) የፕሮጀክቱ ትግበራ (project implementation)
J) ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች (Risk and Assumption)
K) ክትትና ግምገማ (Monitoring and Evaluation)
L) የፕሮጀክቱ ቀጣይነት (sustainability)
እስኪ በዝርዝር እንያቸው

A) ማውጫ (Table of contents)
ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡ ማውጫ ሁሉንም ምዕራፎችና ንዑስ ምዕራፎች ያሉበትን ገፅ ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
B) አጭር መግለጫ (Executive Summary)
ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው ሃሳቦች
☞ ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር
☞ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ
☞ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ
☞የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ
☞ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም
☞ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡
C) መግቢያ (Back Ground)
ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡-
☞ ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ
☞ ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው
☞ ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡

  • ተከታይሽ ሁሉ አድናቂሽ አይደለም
    ተከታይሽ ሁሉ አድናቂሽ አይደለም፡፡ ያሞገሰሽ ሁሉ ያፈቀረሽ አይደለም፡፡ የሳቀልሽ ሁሉ ወዳጅሽ አይደለም፡፡ ትሁት ሁሉ መልካም ሰው አይደለም፡፡ አነጋገሩ የሚያምር ሁሉ አዋቂ አይደለም፡፡ የሰበከሽ ሁሉ ፃድቅ አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያን የሳመ ሁሉ ክርስቲያን አይደለም፡፡ የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም፡፡ ሴትነትሽን ሊያረክስ የሚፈልግ፣ ቀንበጥነትሽን ለመቀንጠስ የሚሽቀዳደም፣ ወጣትነትሽን ሊያኮላሽ ያሰፈሰፈም ከኋላሽ ይከተልሻል፡፡ የሚከተልሽን ሁሉ አትመኚ፡፡ አንዳንዱ ተከታይሽ ከዓላማሽ ሊያደናቅፍሽ፤ ከመንገድሽ ሊያስቀርሽ… Read more: ተከታይሽ ሁሉ አድናቂሽ አይደለም
  • የታላቁ የህዳሴ ግድብ ከፍታ ስንት ነው?
    ግድቡ 645 ሜትር ከፍታ ይኖረዋል ሲባል ከባህር ወለል በላይ የሚኖረው ጠቅላላ ከፍታ ነው።
  • ፈረሰኞቹ ነገ ወደ ታንዛኒያ ያቀናሉ
    በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክለው የቅዱስ ጊዮርጊስ የልዑክ ቡድን ነገ ወደ ታንዛንያ ጉዞ ያደርጋል። የ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ ወር መጨረሻ ለሚኖረው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታ ከሐምሌ 17 ጀምሮ በቢሸፍቱ ከተማ በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ በመከተም ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል። ሶከር ኢትዮጵያ ከሳምንት በፊት ፈረሰኞቹ ነሐሴ ወር መጨረሻ በአፍሪካ በቻምፒዮስ… Read more: ፈረሰኞቹ ነገ ወደ ታንዛኒያ ያቀናሉ
  • የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጥቁሮች ህይወት ያገባኛል በሚል የጀመረውን ድጋፍ እንዲቆም ወሰነ
    የተጫዋቾች መንበርከክ የታሰበውን በጥቁሮች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም ማምጣት ባለመቻሉ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል። የክሪስታል ፓላሱ ቦቲዲቯራዊው የመስመር ተጫዋች በተጠናቀቀው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ከየካቲት ጀምሮ በጉልበቱ መንበርከክ ያቆመ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ አሁንም የዘረኝነት ጥቃቱ ከደጋፊዎች እየደረሰብኝ ነው በሚል ነበር።
  • የ2014 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልዕክት ከዋሽንግተን ዲሲ ሰሜን አሜሪካ።
    እኛም እንደእሷ “አንትሙ ውእቱ ታቦቱ ለመንፈስ ቅዱስ ማለትም እናንተ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናችሁ” ተብለናል፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅደረ መለኮት የሆነችው በሃይማኖት በትሕትና ነው፤ ከዚህ አንጻር እኛም በሃይማኖት ጥላ ሥር ሆነን በትሕትና በፍቅር በአንድነት የምንኖር ከሆነ የእግዚአብሔር ማደሪያ ለመሆናችን ሌላ ምስክር አያስፈልገንም፡፡ ምክንያቱም ጌታችን “ተፋቀሩ በበይናቲክሙ ወእምከመ ተፋቀርክሙ በበይናቲክሙ የአምረክሙ ዓለም በዝንቱ ከመ አርዳእየ አንትሙ፤ እርስ በርሳችሁ አብዝታችሁ ተፋቀሩ፤ እርስ በርሳችሁ ከተዋደዳችሁ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ዓለም በዚህ ያውቃል”


D) ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች (Rationale)
ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግብ
ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡
E) የፕሮጀክቱ ዓላማ (project objective)
ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ
ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡
F) የፕሮጀክቱመግለጫ (project Description)
☞ የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ
☞ ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ
☞ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት
☞ የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት
☞ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ መገለፅ አለበት፡፡
G) የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት (project management and organization)
☞ ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ
☞ የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር
☞ የፕሮጀክቱን ውስጣዊ አሰራር አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መግለፅ አለበት፡፡
H) የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮችና ተጠቃሚዎች (stakeholders and Beneficiaries)
☞ ተጠቃሚዎች (Beneficiaries) ማለት በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ይገልፃል፡፡
☞ ያገባኛል ባዮች (stakeholders):-
የመጀመሪያ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (Primary stake holders)፡-በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው ወይም በፕሮጀክቱ ላይ የሚያደርሱትን ያካትታል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (secondary stake holders)፡- ለፕሮጀክቱ መሰራት የራሳቸው ድርሻና ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ተቋማት ተለይተው መዘርዘር አለባቸው፡፡
I) የፕሮጀክቱ ትግበራ (project implementation)
የፕሮጀክት ዕቅድ ማለት የሚሰሩት ስራዎች፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ የሀብት ድልድል፤ ስራው በማን፤ እንዴት፤ መቼና የት እንደሚፈፀም መገለፅ አለበት፡፡
J) ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች (Risk and Assumption):-
☞ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ስጋቶች ይገለፁበታል፡፡
☞ ለፕሮጀክቱን ተፈፃሚነት የሚያፋጥኑ፤ የሚረዱ በጎ ጎን ያላቸው ነገሮች አብራርቶ በሰንጠረዥ መገለፅ አለበት፡፡
K) ክትትና ግምገማ (Monitoring and Evaluation):

☞ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፤ የስራ ጉብኝት፤ የማማከር ስራ መቸ እንደሚደረግና በስንት ጊዜ ልዮነት እንደሚቀርብ
☞ የክትትል ስራ የሚሰራበት ስልት
☞ የግምገማ ዕቅድን
☞ ፕሮጀክት እንዴት ለሚመለከታቸው ሪፖርት እንደሚደረግ
L) የፕሮጀክቱ ቀጣይነት (sustainability):
ፕሮጀክቱ የሚሰጠውን ጥቅም ዘላቂነት መገለፅ አለበት፡፡

Discover more from Mahidere Tsibeb

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading

Design a site like this with WordPress.com
Get started