

“በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን”
ከባህርዳር ከተማ ተነስተው ወደ ሰሜን አቅጣጫ በጣና ሀይቅ ላይ በጀልባ እየተጓዙ እንዳሉ በደን የተሸፈነችውን ታለቋን የዘጌ ገዳምን ማየት ይጀምራሉ። ከዚያም ለአንድ ሰዓት ተጉዘው የባህር ላይ ጉዞውን በማጠናቀቅ በመንበረ ብርሃን አዝዋ ቅድስት ማርያም ገዳም ለጀልባዎች መጠጊያ በተዘጋጀው ወደብ ይደርሳሉ። ከወደቡ ተነስተው ለሶስት ደቂቃ ያክል በእግር እንደተጓዙ ጥንታዊና ታሪካዊ ከሆነችው በመንበረ በርሃን አዝዋ ቅድስት ማርያም ገዳም ይደርሳሉ።
ገዳሟ የተመሰረተችው በ1307 ዓ.ም በአፄ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት ሲሆን፣ ገዳሙን የመሰረቱት አባት አቡነ በትረ ማርያም ናቸው። የአባታችን አቡነ በትረ ማርያም ሀገራቸው ቅዱሳን በብዛት ከተገኙበት የሸዋ ምድር ነው። ከአባታቸው ተክለማርያም ፣ እናታቸው ኢላሪያ ይባላሉ። እነዚህም የተባረኩ ሰዎች እግዚአብሔር ባዘዘው በወንጌል ህግ እየተመሩ፣ እግዚአብሔርንና እናቱን ድንግል ማርያምን የሚወዱ፣ እንግዳ የሚቀበሉ፣ የተራበ የሚያበሉ፣ የተጠማ የሚያጠጡ፣ የተራዘ የሚያለብሱ፣ በጾምና በጸሎት ሌትና ቀን ወደ እግዚአብሔር ይማልዱ የነበሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ።
እግዚዚጾማቸውንና ጸሎታቸውን ተቀብሎ ከእለታት አንድ ቀን ተኝተው ሳለ ኢላሪያ ራዕይ አየች። ተክለ ማርያምም በተመሳሳይ ራዕይ አየ። እግዚአብሔርም መልአኩን ወደ እነሱ ላከና የተባረከና የተቀደሰ ደግ ልጅ እንደሚወልዱና ልጁም የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንደሚሆን፣ በወንጌል ያላመኑትን ሰዎች በወንጌል ስብከት ወደ እግዚአብሔር እንደሚያቀርባቸው እና የተቸገሩትን ህሙማን በጸሎት እንደሚፈውሳቸው፣ የአዘኑትን እንደሚያጥናናቸው፣ የተለያየ ተአምራትን እንደሚያደርግና እንደሚሰራ በራዕይ ታያቸው።
- ተከታይሽ ሁሉ አድናቂሽ አይደለምተከታይሽ ሁሉ አድናቂሽ አይደለም፡፡ ያሞገሰሽ ሁሉ ያፈቀረሽ አይደለም፡፡ የሳቀልሽ ሁሉ ወዳጅሽ አይደለም፡፡ ትሁት ሁሉ መልካም ሰው አይደለም፡፡ አነጋገሩ የሚያምር ሁሉ አዋቂ አይደለም፡፡ የሰበከሽ ሁሉ ፃድቅ አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያን የሳመ ሁሉ ክርስቲያን አይደለም፡፡ የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም፡፡ ሴትነትሽን ሊያረክስ የሚፈልግ፣ ቀንበጥነትሽን ለመቀንጠስ የሚሽቀዳደም፣ ወጣትነትሽን ሊያኮላሽ ያሰፈሰፈም ከኋላሽ ይከተልሻል፡፡ የሚከተልሽን ሁሉ አትመኚ፡፡ አንዳንዱ ተከታይሽ ከዓላማሽ ሊያደናቅፍሽ፤ ከመንገድሽ ሊያስቀርሽ… Read more: ተከታይሽ ሁሉ አድናቂሽ አይደለም
- የታላቁ የህዳሴ ግድብ ከፍታ ስንት ነው?ግድቡ 645 ሜትር ከፍታ ይኖረዋል ሲባል ከባህር ወለል በላይ የሚኖረው ጠቅላላ ከፍታ ነው።
- ፈረሰኞቹ ነገ ወደ ታንዛኒያ ያቀናሉበአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክለው የቅዱስ ጊዮርጊስ የልዑክ ቡድን ነገ ወደ ታንዛንያ ጉዞ ያደርጋል። የ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ ወር መጨረሻ ለሚኖረው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታ ከሐምሌ 17 ጀምሮ በቢሸፍቱ ከተማ በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ በመከተም ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል። ሶከር ኢትዮጵያ ከሳምንት በፊት ፈረሰኞቹ ነሐሴ ወር መጨረሻ በአፍሪካ በቻምፒዮስ… Read more: ፈረሰኞቹ ነገ ወደ ታንዛኒያ ያቀናሉ
አንድ ቀን እግዚአብሔር በአዘዘው ሕገ ክርስቶስ ስጋውን እና ደሙን ተቀብለው እግዚአብሔር ባዘዘው ትዕዛዝ መሰረት ተወስነው በአንድ ሲኖሩ በነሀሴ ወር ተክለማርያም ኢላሪያን በግብር አወቃትና በዚህ እለት ፀንሳ አቡነ በትረ ማርያምን ግንቦት 21 ቀን ወለደች። ወላጆቹም በመካንነት ይኖሩ ስለነበር እግዚአብሔር ልጅ ስለሰጣቸው ለኛ ጧሪ፣ ቀባሪና ደጋፊ (ምርኩዝ) ይሆናል በማለት ስሙን በትረ ማርያም አሉት። በትረማርያም ሰባት አመት እስኪሞላቸው ድረስ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከቆዩ በኋላ ወላጆቻቸው ወደ ኤዎስጣቴዎስ ገዳም መንፈሳዊ ትምህርት ቤት አስገቧቸው።
በገዳሙ ባሉት መነኮሳት ዘንድ እንጨት በመልቀም፣ ውሃ በመቅዳት እያገለገሉ የብሉይና የሀዲስ ኪዳን መፃህፍትን በመማር አደጉ። በዚህ ጊዜ ትህትናቸውንና እውቀታቸውን ያዩ አጋንንት አጥብቀው ይዋጓቸው ነበርና፣ የአጋንንት ፈተና ሲፀናባቸው ወደ ገዳሙ መምህር ሄደው አጋንንት እንደሚፈታተኗቸው ተናገሩ። የገዳሙ መምህርም መንኩስና አስኬማንና እንዲሁም ክህነትን ብትቀበል አጋንንትን በክህነትህ ታወግዛቸዋለህ አሏቸው። እርሳቸውም በታዘዙት መሰረት ወደ አቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም ሄደው ከአባ ዜና ማርቆስ አስኬማ ከተቀበሉ በኋላ ወደ ሊቀ ጳጳሱ ሄደው ረቡዕ ዕለት ቅስናን አርብ ቀን ቁምስናን ተቀብለዋል። በዛውም ገዳም የብሉያትንና የሀዲሳትን መፃህፍት በማስተማር አገልግለዋል። ከዚያም በኋላ “ስለፅድቅ የሚሰደዱ ንዑዳን ክቡራን ናቸው። መንግስተ ሰማያትም የእነርሱ ናትና” /ማቴጨ3:10/ ባለው ቃል መሰረት ከሀገር ወደ ሀገር እየተዘዋወሩ በገድላቸው ላይ ተፅፎ እንደሚገኘው በጎጃምና በጎንደር ወንጌልን አስተምረዋል። ከዚያም ህሙማንን እየፈወሱ፣ ያዘኑትን እያረጋጉ፣ ለሁሉም ወንጌልን እያስተማሩ ስድስት አመት ከሞላቸው በኋላ፣ በእግዚአብሔር ፍቃድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ሰብሳቢነት ከስድስት መንፈሳዊ ወንድሞቻቸው ጋር ተገናኙ።
ስድስት የተባሉት ወንድሞቻቸውም:-
- አቡነ ሂሩተ አምላክ……..ዘዳጋ እስጢፋኖስ
- አቡነ አሳይ……………….ዘመንዳባ
- አቡነ ዘካሪያስ……………ዘገሊላ
- አቡነ ይፍቅረነ እግዚእ…..ዘጉቤ
- አቡነ ታዲዎስ…………….ዘደብረ ማርያም
- አቡነ ዘዮሐንስ…………….ዘክብራን
ከእነዚህ ወንድሞቻቸው ጋር ተገናኝተው መንፈሳዊ ነገርን ከተነጋገሩ በኋላ፣ የጣና ሀይቅ ደረቅ ምድር ሆኖላቸው ባህሩን በታምራት እየረገጡ ዳጋ እስጢፋኖስ ከተባለው ደሴት ገዳም ገቡ። በዚያም ገዳም የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስን አርባዋን ፆም ከፆሙ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተገልፆ እንዲህ አላቸው፣ “ለአንተ የተፈቀደልህ ይህ ገዳም አይደለምና ከዚህ ተነስተህ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ ምትታየው ደሴት ሂድ” አላቸው። እርሳቸውም በታዘዙት መሰረት በገድላቸው ላይ ተፅፎ እንደሚገኘው ተአምር ቀሚሰሩባት በትር ሆነው፣ በትሯም እንደ ታንኳ ሆናላቸው እንደ እስራኤል ልጆች (ዘፀዐ 19:26) መልዓኩ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ዛሬ ማይ መቅጃ እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ደረሱ። ከደሴቱ ትንሽ ወጣ ብለው በአሁኑ ሰዓት የእመቤታችን ቤተክርስቲያን ከሚገኝበት ቦታ ቆመው ሲፀልዩ ብርሃን ታያቸው፣ ለዚህም ነው የቦታው ስያሜ “መንበረ ብርሃን” ተብሎ የተሰየመው፣ እንደዚሁም ቁመው ሲፀልዩ ከእግራቸው ስር ደዌ የሚፈውስ፣ እውር የሚያበራ፣ ለምፅ የሚያነፃ፣ አጋንንትን የሚያወጣ ብዙ ተአምራት የሚሰራ ፀበል ፈልቆላቸዋል።

ከዚህም በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ በአራቱ ማዕዘናት የሚመጡ ህሙማንን በፈለቀው ጠበል የሚፈወሱ ሆነዋል። በዘጌ ገዳም ውስጥ እየተዘዋወሩ ሲፀልዩ፣ አራራት እየተባለ አሚጠራው ተራራ ላይ ሆነው በአራት አቅጣጫ ለኖህ የሰጠኸውን ቃል ኪዳን አስብ፣ ሀገሪቱን ከጥፋት ጠብቅ፣ እያሉ በሚፀልዩበት ጊዜ፣
ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ላይ ሆኖ ተገልፆ እየመራ ወስዶ ቤተክርስቲያኔን የምትሰራ እዚህ ቦታ ላይ ነው አለና በፈረሱ ኮቴ በተአምራት ድንጋዩን እንደ ሰም አቅልጦ ምልክት አደረገና አሳያቸው። በዚህ ቦታ ላይም የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተክርስቲያን መሰረቱ። ከዚህ በኋላ ከዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም መጥተው ካረፉባት የስዕል ቤታቸው የነበረችውን የእመቤታችን ቤተከርስቲያን አድርገው ሰርተው የመንበረ ብርሃን አዝዋ ማርያም ገዳምን መስርተዋል።
አባታችን አቡነ በትረ ማርያም ከ8እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ሲሄዱ የሚያርፉበት ቦታ “አባ በፀሎት” እየተባለ ይጠራል። ብዙውን ጊዜ የሚቀመጡት በእመቤታችን ቤተከርስቲያን ስለነበር በዘመኑ የነበረው ንጉሥ የሚያደርጉት ተአምራትንና ቅድስናቸውን ሰምቶ ሂዳችሁ የአሉበትን ቦታ አይታችሁ ኑ፣ ከዚያ በኋላ እኔ እሄዳለሁ ብሎ ሰራዊቱን ልኮ ነበርና የንጉሡ ሰራዊቶች እየፈለጉ መጥተው በጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ያሉትን መነኮሳት አባታችን ወዴት ነው ያሉ ብለው ጠየቋቸው። መነኮሳቱም “እዚያ” ነው ያሉ፣ ብለው መለሱላቸው፣ እዚያ በአሏቸው ቃል መሰረት በኢትዮጵያ ባህል አጠራር እንዲመች የገዳሟ ስም አዝዋ ተባለች።
በ1289 ዓ.ም የነገሰው የኢትዮጵያ ንጉሥ አፄ አምደ ፅዮን የላካቸው ሰራዊት ሂደው ቅድስናቸውንና ፀሎታቸውን፤ ትህትናቸውንና ፍቅራቸውን፤ እንዲሁም የገዳሟንና የቦታዋን ማማር በነገሩት ጊዜ ብዙ ሰራዊት አስከትሎ ወደ ዘጌ ገዳም መጣና ከአባታችን ከአቡነ በትረ ማርያም ጋር ተገናኝቶ ቡራኬ ተቀብሎ ሀገሩንና ሰራዊቱን ከባረኩና ስለ ኃይማኖት ብዙ ከተነጋገሩ በኋላ ለንጉሱና ለሰራዊቱ ማረፊያ የሚሆኑ ቦታ ከአዝዋ ማርያም ቀረብ ያለ ቦታ ሰጧቸው።
ንጉሥ አምደ ፅዮንም ከአባታችን ከአቡነ በትረ ማርያምና በዘጌ ገዳም ፈፅሞ ስለተደሰተ፣ የገዳሟንም ስም “እርዘ ሊባኖስ” ብሏታል ። እርዘ ሊባኖስ ያሉበትም ምክንያት በደጋ የሚያስደስት ዝግባና ፅድ እንደሚገኝ ሁሉ፣ በዘጌ ገዳም ውስጥም እንደዚሁ ዛፎችና የተለያዩ እፅዋቶች ስለሚገኙበትና በደን የተሸፈነች ገዳም ስለሆነች ነው። ንጉሥ አምደ ፅዮንም በአዝዋ ማርያም ገዳም አጠገብ ሰራዊቱን አስፍሮና ከአባታችን ከአቡነ በትረ ማርያም ቡራኬ እየተቀበለና ከገዳሟ እየተሳለመ ስለኖረ የንጉሡ አምደ ፅዮንም ገዳሙም ደብሩም ናት እየተባለች ትናገራለች። ለዚህም ማስረጃ የሚሆን በገዳሙ የኖሩ የድሮ ቅዱሳን አባቶች የደረሱት ድርሰት እንዲህ ይላል። “ኢይኪድዋ ለእየሩሳሌም እለእኩየ መከሩ፣ እቅብዋ ጻድቃን እለ ሰናየ ትነብሩ እንዘትብሉ በቃል እንዘ ታዜክሩ አርዘ ሊባኖስ ለበትረ ማርያም መቃብሩ ወመንበር ብርሃን ለአምደ ጽዮን ገዳሙ ወደብሩ” ይህ ማለትም “የእየሩሳሌም ክፍያ የተባለች ዳግማዊት እየሩሳሌም ዘጌን እርሷን ለማጥፋት ክፉ የሚመክሩ ሰዎች እንዳይረግጧት በበጎ እረፍት የምትኖሩ ጻድቃን ሆይ ጠብቋት። በቃል እየተናገራችሁና እያሳሰባችሁ አርዘ ሊባኖስ የተባለች ዘጌ የበትረ ማርያም መቃብሩ የብርሃን መቀመጫ የተባለች አዝዋ ማርያም የንጉሥ አምደ ፅዮን ደብሩም ገዳሙም ናትና” ብለው ተናግረዋል።
ይሄሁየአርኬ ድርሰት አዝዋ ማርያም ከሚገኘው መቅደም ወንጌል ተመልከት። ከአባታችን ከአቡነ በትረ ማርያም ለ23 አመት በፆም በጸሎት ተወስነው ከኖሩ በኋላ በገድላቸው ውስጥ ተዘርዝሮና ተፅፎ እንደሚገኘው ከፈጣሪያቸው ብዙ ቃል ኪዳን ተቀብለው በ 89 ዓመት ተኩል እድሚያቸው ሐምሌ 17 ቀን አርፈዋል።
=========ስዕል በቤተ-ክርስቲያን=======
ስዕል ከእግዚአብሔር የተሰራ መሆኑንና እግዚአብሔር በስዕሉ ላይ አድሮ እንደሚያናግርና እንደሚናገር ቅዱሳን መጻሕፍት ያስረዳሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኦሪት ዘጸአት በምዕራፍ 25፤18 ላይ እንደተፃፈው እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ሁለቱን ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፣ በስርዓት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ፣ ከስርዓት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን ሁለተኛውን ኪሩብ በሌላ ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሰራዋለህ፣ ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ የስርዓት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፣ ፊታቸውም እርስ በእርስ ይተያያል፣ የኪሩቤልም ክንፎቻቸው ወደ ስርዐት መክደኛው ይመለከታሉ የስርዓት መክደኛውን በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ፣ በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ የእስራኤልንም ልጆች ታዝ ዘንድ የምሰጥህን ሁሉ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል በስርዓት መክደኛው ላይ ሁኘ አነጋግርሃለሁ” ሲል ያስረዳል። (ኦሪት ዘጸአት እስከ ቁጥር 22 ድረስ ተመልከት)
ጌታችን እንዲህ ብሎ በአዘዘው ህግና ስርዓት በዓመት አንድ ቀን ሊቀ ካህናቱ ከቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ገብቶ ከሁለቱ ኪሩቤል መካከል ድምፅ ሰምቶ ይወጣ ነበር። ጌታችን በሁለቱ ኪሩቤል በስርየት መክደኛው መካከል ለሙሴ ሲያነጋግረው እንደነበር ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ ባሉ በእርሱ ስምና በእናቱ በድንግል ማርያም ስም፣ በነቢያትና በኃዋሪያት፣ በሰማዕታትና በፃድቃን ስም በተሳሉ ስዕሎች አድሮ፣ ስዕሎችም እንደሚያናግሩና ተዓምራት እንደሚሰሩ፣ ከፊታቸው ቀርበው ቢለመኑ ልመናን እንደሚሰሙ ከላይ የተጠቀሰው ቃል ያስረዳል። በዚህ መሰረት በቤተ መቅደሱ ዙሪያ የጌታችንና የመድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ የቅዱሳን መላዕክት የፃድቃንና የሰማዕታት፣ የሐዋርያት ስለ ኃይማኖታቸው የተቀበሉትን መከራ፣ ተጋድሎአቸውንና ያገኙትን ክብራቸውን በጥንታዊ ሰዓሊያን በስዕል ተገልፆ ይገኛል።
===========ስዕለ ሉቃስ============
በነገረ ማርያም እና በተአምር ማርያም ተፅፎ እንደሚገኘው ሉቃስ ከሳላቸው ስዕሎች አንዲቱ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ገበያ ወጣች። መስከረም 10 ቀን በሚነበበው ነገረ ማርያም እንዲህ ይላል። በዚያን ወራት የእግዚአብሔር እና የእናቱ የድንግል ማርያም ወዳጅ ከሆነች የኢትዮጵያ ሀገር አንድ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ ኢየሩሳሌምን ለመሳለም ሲሄድ በሶሪያ ያሉትን ገዳማት ለመሳሌወደ ሶሪያ አገር ሄደ። በዚያም ጸደኒያ በሚባል ቦታ አንድ የደናግል ገዳም እመምኔት ከገዳሙ ውስጥ የእንግዳ መቀበያ ቦታ ነበራትና የወጣ የወረደውን፣ ያለፈ ያገደመውን፣ እንግዳ ሁሉ ትቀበል ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ቴዎድሮስ የተባለው ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ከቤቷ ተስተናግዶ አደረ። የመሪናም ልማዷ ከእንግዶች ትምህርትና ምክርን እንዲሰጧት ትጠይቅ ነበርና አባ ቴዎድሮስም ከአስተማራት እና ከመከራት በኋላ እንዲህ አላት፣ “ከፈተና የምትጠብቅ፣ ከሀዘን የምታረጋጋ የእመቤታችን ስዕል በእየሩሳሌም አለችልሽና እሷን አስመጭ አሏት።” መሪናም እሷን ማን ያመጣልኛል? አለችው እሱም እኔ ወደ እየሩሳሌም እሄዳለሁና እኔ አመጣልሻለሁ አላት። እንግዲያውስ ገንዘብ ልስጥህ አለችውደ እሱም በእኔ ገንዘብ ገዝቸ አመጣልሻለሁ፣ አለና ወደ እየሩሳሌም ሄደ። በእየሩሳሌም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ታዕምራት ያደረገባቸውን ቦታዎች ወደ ሀገሩ ሲመለስ “ያች ሴት ያዘዘችህን ስዕል ለመግዛት ለምን እረሳህ” የሚል ድምፅ ከወደ ሰማይ ሰማ፣ ከዚያም ደንግጦ ወደ ገበያ ወጣና ስዕል ወደሚሸጥበት ቦታ ሄዶ ታምረኛዋን ሉቃስ የሳላትን ስዕል አግኝቶ ገዛና በመሀረብ ጠቅልሎ መንገዱን መጓዝ ጀመረ። አንበሳ ከዱር ወጣና ሊጣላው ሲል ገባሪተ ሀይል የሆነችው ስዕሊቱ አፍ አውጥታ ድምፅ አሰምታ ከአንበሳው አስጣለችው። በዚህ እየተደነቀ መንገዱን ሲሄድ ሁለተኛ ወንበዴዎች ሊጣሉት ቢመጡ ስዕሊቱ እንደ መብረቅ የሚያስፈራ ድምጥ አሰምታ አባረረቻቸው።
ኢትዮጵያዊ አባ ቴዎድሮስም ከብዙ ፈተና የምትጠብቀውን የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ስዕል ለሌላ ሰው የምሰጥ ለእኔ ምን ይዤ አለና ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ በቀይ ባህር ወደብ ተሳፈረ። እግዚአብሔርም የእናቱን የድንግል ማርያም ስዕል ወደ ወዳጁ መሪና ቤት ሄዳ ነአምራት እንድታደርግ ፈቃዱ ነውና፣ ነፋስ አስነስቶ ማዕበል አባ ቴዎድሮስ የተሳፈረበትን ጀልባ (መርከብ) ወደ ሶሪያ ወሰዳት። አባ ቴዎድሮስም ከመርከቡ ከወጣ በኋላ ሲመሽ የሚያድርበት ቤት ስላጣ መቸም አታውቀኝም በማለት ወደ መሪና ቤት ሄዶ አደረና ሲነጋ ወጥቶ ለመሄድ ቢሞክር አዕምሮው ተነስቶት /ተስቶት/ የገዳሙን ግቢ ይዞር ጀመረ።
የመሪናም አይታ አዘነችና አባቴ ሆይ ደክሞሀልና አድረህ ትሄዳለህ አለችውና አደረ። መሄድም አልሆንለት ብሎ እስከ ሶስት ቀን እንዲህ እያደረገ ቆየ። መሪናም በሶስተኛው ቀን አባቴ ሆይ አዕምሮህ ተነስቶህ አያለሁና ያደረከው ነገር ምንድን ነው? አለችው። እሱም እግዚአብሔር እንዳልሰደደው፣እመቤታችንም ታዕምራቷን እንደገለጸችበት አይቶና ተረድቶ ታሪኩንና ስዕሊቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ያደረገችውን ሂደትና ታዕምራት ተናግሮ፣ ስዕሊቱን ለመሪና ሰጣት። የመሪናም ከፍቅሯ ብዛት የተነሳ እያለቀሰች ስዕሊቱን ተቀበለች። አባ ቴዎድሮስም ለመሪና ስዕሊቱን የሰጠበት ቀን መስከረም 10 ነው። መሪናም በገዳሙ ውስጥ ለስዕሊቱ ልዩ ቦታ ሰጥታ አስቀመጠቻት። በስዕሊቱ ፊት ሌሊትና ቀን መብራት ይበራ ነበር። አባ ቴዎድሮስም ያችን ስዕል እያገለገለ እስከ ሚሞትበት ቀን ድረስ በዚያ ቦታ በገዳም ኖረና፣ ሲያርፍ በእመቤታችን አማላጅነት ወደ መንግስተ ሰማያት ገባ። የመሪናም እሱን ተከትላ አርፋ ወደ መንግስተ ሰማያት ገባች።
ከዚህ በኋላ ያችን ሰዕል በክብር ወደ ገዳሙ ቤተከርስቲያን ውስጥ አግብተው አስቀመጧትና በሌሊትና በቀን ወዝ የሚወጣት ሆነ። ይህን ተአምር የሰማ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ወደ ሶሪያ አገር ተጉዞ ከገዳሙ ደረሰና ቤተከርስቲያኑን ተሳልሞ ስዕሊቱን ሊሳለም ወደ ስዕሊቱ ሲሄድ ከፊቷ ወዝ ሲወጣ አይቶ አደነቀና ይህ በከንቱ መፍሰስ የለበትም ለህሙማን ድህነት እንዲሆን በክብር ይቀመጥ ብሎ አዘዘ። እነሱም ዕቃ አምጥተው ከስዕሏ ስር አደረጉና ወዟ እየተንጠፈጠፈ በእቃው ይሞላ ጀመር። የታመሙ ሰዎችም ያንን እየተቀቡ ከተለያዩ ደዌ የሚድኑ ሆኑ። ህሙማኑን ለማዳን አባ ዘጊዮርጊስ እንዲህ ብሎ ተናግሯል፣
“ሰላም ለእስልኪ እንተ ሰአላ በእዱ ሉቃስ ጠቢብ እም ወንጌላውያን አሐዱ እምአም ተቀቡ ማርያም እምአፍ ስእልኪ ቅብአ ናርዱ በህማም እኩይ እለ ደወዩ ወዉህዱ ፅዑራነ ምድር ጥእዩ ፈድፈዱ”። ይህም ሲተረጎም
“ከወንጌላውያን አንዱ ጥበበኛው ሉቃስ በእጁ ለሳላት ስዕል ሰላምታ አቀርባለሁ፣ ማርያም ሆይ የሽቱ ቅባት ከሚፈሰው ከስዕልሽ ወዝ በተቀቡ ጊዜ የምድር ተጨናቂዎች ህሙማን ድነው እጅግ በዙ ይላል።”
እንግዲህ የእመቤታችን የድንግል ማርያም ስዕል ከተለያዩ ደዌ እንደምታድን ቅዱሳን አባቶች ለብዙ ዘመን ተናግረዋል። ወደ እስክንድርያ ጳጳስ ታሪክ እንመለስና ክብረ በዓሏን ካከበረ በኋላ ለዚያች ስዕል ከሶሪያ ክርስቲያን ከገዳመ መነኮሳት ደናግል ጋር እንዲህ ሲል ስርዓት ሰራላት። መሪና ታደርገው የነበረውን በሌሊትና በቀን ከፊቷ መብራት እንዲበራላት፣ ስዕሏን የምታገለግላትና በክብረ በዓል ጊዜ ለማውጣት ሲፈለግ ድንግል የሆነች ሴት መነኩሴ ይዛት እንድትወጣ ስርዓት ሰርቶላታል።
እንዲህ ሆና ስትኖር የስዕሏን ታምር የሰሙ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት፣ ካህናትና ዲያቆናት ወደ ሶሪያ ሂደው ለስዕሊቱ ሰግደው እጅ በነሷት ጊዜ፣ እናንተ ኢትዮጵያዊያን ወዳጆቸ ሆይ እንኳን ደና መጣችሁ፣ እኔ እኔ እንደምወዳችሁ እናንተም ትወዱኛላችሁን? ብላ ስዕሊቱ አፍ አውጥታ ተናግራቸዋለች።
በሀገራችን የነገሱት አፄ ዳዊት የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስን መስቀል ለማምጣት አስበው ይዘው ሲመጡ ካርቱም ላይ ሲሞቱ፣ ከመስቀሉ ጋር ብዙንዋየ ቅድሳትና ይህች ስዕል፣ ሌሎች ቅዱስ ሉቃስ የሳላቸው 3 ስዕሎች አብረው መጥተዋል። በኋላም ልጃቸው አፄ ዘርአያቆብ ነግሰው ካርቱም ላይ ያለውን መስቀሉንና ንዋየ ቅድሳቱን ወደ ኢትዮጵያ ሲያመጡ፣ ይህች ስዕልና ሌሎች ቅዱስ ሉቃስ የሳላቸው 3 ስዕሎች አብረው ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል። ይህ በእንዲህ እያለ ከነዚህ 4ቱ ስዕሎች አንዲቱ በኢትዮጵያ ነገስታት ቤት ስትቀር ሌሎች ሶስት ስዕሎች መስቀሉን ለማምጣት አብረው ለሄዱት ቅዱሳን አባቶች ሲሰጡ አንዲቱ ለአቡነ በትረ ማርያም ተሰጥታቸዋለች። እሳቸውም አምጥተው በመንበረ ብርሀን አዝዋ ማርያም ገዳም ውስጥ አስቀምጠዋት ትገኛለች።
ስዕሏም በዚህ ገዳም ውስጥ ያደረገችው ድንቅ ታምር የሚከተለው ነው:-
1ኛ. አቡነ በትረ ማርያም ሲሰግዱ እና ሲፀልዩ ታነጋግራቸው እንደነበር እመቤታችን የበረከት ፅዋ ትሰጣቸው እንደነበር
2ኛ. የቀደሙ አባቶች ቤተከርስቲያን ስለው ከጨረሱ በኋላ በተለያዩ ቀለማት ስዕሊቱን እናሳምራለን እያሉ ሰዓሊው ለመሳል ሲሞክር፣ ስዕሊቱ አፍ አውጥታ ከነበረው ውጭ እንዳይነካካ እንደገሰጸቻቸው
3ኛ. ስዕሊቱ የምትቀመጠው በቤተክርስቲያን ስርዓት ስዕለ ማርያም በምትሳልበት በኩል ነበር። ከእለታት አንድ ቀን አንድ የውጭ ጎብኝ ቤተክርስቲያኗን ሲጎበኝ የስዕሏን ፎቶ ሊያነሳ ሲል መነኮሳት አባቶች ማንሳት ክልክል ነው ቢሉት ቃላቸውን ባለመስማትና ባለማክበር ሊያነሳት ሲል በአለበት ቦታ ተንቀጥቅጦ ታሞ እንደወደቀ
4ኛ. በአሁኑ ሰዓትም በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስዕል እየተማጸኑ ፀሎት እያቀረቡ ተማፅኖአቸውንና ፀሎታቸውን እመቤታችን እየተቀበለቻቸው፣ መካኖች ልጅ እያገኙ፣ ህሙማን ከደዌአቸው እየተፈወሱ ይገኛሉ።
👉ይህች ስዕል መስከረም 10 ቀን በመነኮሳት ተይዛ ወጥታ ለሁሉም ምዕመናን ትታያለች።
የቤተክርስቲያኗ የንግስና አመታዊ በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል።
1ኛ. መስከረም 10 ቀን:- በዓለ ጼዴንያን ይከበራል።
2ኛ. ታህሳስ 3 ቀን:- በዓለ በዓታ ለማርያም ይከበራል።
በገዳሟ ውስጥ ካሉ ቅርሶች መካከል:-
- የብር ጥላ
- የተለያዩ አክሊሎች
- የተለያዩ የብራና መፅሀፍት
- ሰባት መቶ አመት የቆየ ስን
- ፅንሀህ
- የወርቅና የብር መስቀሎች
- ከጉማሬ ቆዳና ከወርቅ ቅብ የተሰራ ጋሻ
- የብርና የወርቅ ካባዎች
- የብር ፅዋዎች
Leave a comment