Category: ግጥም

  • የሰፋ ሀገር ይዘን፣ ጠቦ መሞት ይብቃን (ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ)

    የበላ እያሠረ – የቀማ ቢገፈው፣ የሳተ እያረመ – ያጠፋ ቢገርፈው፤ ጀግና ልማዱ ነው፣ ባርያ ሆኖ ታሽቶ፣ ንጉሥ ኾኖ መግዛት፣ እያነሰ ገዝፎ – እየሞተ መብዛት፤ ያ ሽንታም ላመሉ – በሬሳ ይፎክራል፣ ከፈሪ ገዳይ ‘ድል’ – የጀግና ‘ሞት’ ያምራል፤

  • ኅሊና ደሳለኝ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በቤተ መንግስት ያካቀረበችው ግጥም

    የማጀት ስር ወንጌል ሙያተኛ ሀገሬ ከማጥገብ ጎደለ በረከት እራቀው የገበታሽ ለዛ፣ተሻምቶ ለመጉረስ ከበላነው ይልቅ የደፋነው በዛ፡፡ሙያሽ ባያስደፍር አጀብ ቢሰኙበት፣ማዕዱ ቢሙላላ ዓይነቱ ቢያምርበት፣አበዛዙ አይደለም አበላሉ ላይ ነው የገበታሽ ውበት፡፡እየተማመንን! የፉክክር ቅሚያ በርሃብ እየናጥን፣ከደፋነው ጠግቦ ውሻችን በለጠን፡፡ከምርት አላነስን፣ጎተራችን ሙሉ ጀግና አራሽ መች አጥተን፣ማሰብ የጎደለው አያያዛችን ነው ገደል የከተተን፡፡ይልቅ ግዴለሽም! ከምግባር ምጣድ ላይ ሳንበስል አንጋግተሸ ከማዕድአትምሪን፣ገበታሽ እንዲያምር ከእግዜር…

Design a site like this with WordPress.com
Get started